ከኦገስት 18 እስከ 22 ቀን 2025 ዓ.ም. በቤልጅየም ፍሌሚሽ እና በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የድህረ-ምረቃ (PhD) ልምድ ልውውጥ ወርክሾፕ የተሳተፉ ከሰባት የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ምሁራን በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በመገኘት ከክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ጋር ስለቆይታቸው ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

ከኦገስት 18 እስከ 22 ቀን 2025 ዓ.ም. በቤልጅየም ፍሌሚሽ እና በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የድህረ-ምረቃ (PhD) ልምድ ልውውጥ ወርክሾፕ የተሳተፉ ከሰባት የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ምሁራን በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በመገኘት ከክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ጋር ስለቆይታቸው ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
አምባሳደር እሸቴ በመጪው አመት በሚከበረው የኢትዮጵያና ቤልጅየም የዲፕሎማሲ ግንኙነት 120ኛ ዓመት ክብረ- በዓል የትምህርት ዘርፍ ትብብርን መዘከር እንደሚገባና ክብረ-በዓሉ ትብብሩን በሚያሳይ መልኩ መከበር እንዳለበት አንስተዋል። ከትብብሩ የተገኘውን ልምድ ወደሁሉም ዩኒቨርሲቲዎቻችን ማስፋት ጠቃሚ መሆኑን የሁለቱ ወገን የፕሮግራም አስተባባሪዎች ገልፀዋል።
Professors from seven Ethiopian Universities who took part in the Flemish–Ethiopian Postgraduate (PhD) Experience sharing Workshop, held from August 18 to 22, 2025, visited the Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in Brussels. The Professors and engaged in discussions with H.E. Ambassador Eshete Tilahun to reflect impression of their mission.
Ambassador Eshete emphasized the importance of further strengthening the cooperation in the higher education and of showcasing such collaboration as part of the upcoming celebration of the 120th Anniversary of Ethiopia–Belgium diplomatic relations. Coordinators of the programmers for both sides emphasized the importance of scaling up the Doctoral Degree Programs.